Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Well Come / እንኳን ደሀና መጡ/

Home

Location

መግቢያ /introduction/

የአንድ ሀገር የአካባቢ ልማት ደረጃ የሚገለጽባቸዉ ሁኔታዎች በርካታ ቢሆኑም በዚህ መጽሄት ላይ ወረዳዉ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ አንዳንድ የልማት አመልካቾች በትንተና ለማጠናከር ጥረት የተደረገ ሲሆን በመጽሄቱ የተለያዩ ክፍሎች ዉስጥ የስነ ህዝብ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ግንባታ ሂደት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ አመልካቾች ተካተዋል

ወረዳዊ ሁኔታ

ኤፍራታ ግድም ወረዳ በአ///መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር ካሉት 27 ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ወረዳዉ ከዞን ርእሰ ከተማ /ብርሀን 140 . ከክልል ርእሰ ከተማ ባህር ዳር 840 . ከሀገራችን ርእ4 ከተማ አዲስ አበባ 271 . ርቀት ላይ ይገኛል፡፡የወረዳችን አዋሳኝ ወረዳዎች ስንመለከት በሰሜን አንጾኪያ ገምዛና አርጡማ ፉርሲ ወረዳ፣በደቡብ ቀዎት፣ በምስራቅ ጅሌ ጥሙጋ በምእራብ ከመንዝ ጌራ እና ከመንዝ ማማ ወረዳወች ይዋሰናል ወረዳዉ 18 ገጠር ቀበሌ እና 2 የከተማ ቀበሌ በጠቅላላ 20 ቀበሌዎች የተዋቀረ ነዉ፡፡የወረዳዉ የቆዳ ስፋትም 72682 / ነዉ ፡፡የብሄር ብሄረሰብ መረጃ ስናይ 98.6 የአማራ ብሄረሰብ 0.98 የኦሮሞ 0.2አርጎባ እና0.4 ሌሎች ሲሆኑ የሃይማኖት አይነቶች ኦረቶዶክስ ፣እስልምና ፣ካቶሊክ ፣ፕሮቲስታንት፣ የመሳሰሉት ይከተላሉ፡፡ የወረዳዉ ህዝብ

.

ወንድ

ሴት

ድምር

%

2004

ገጠር

48739

47963

96702

95.52

ከተማ

2155

2385

4540

4.48

ድምር

50894

50348

101242

100

2005

ገጠር

49480

48685

98169

93.38

ከተማ

2248

2487

4735

6.62

ድምር

51728

51176

102900

100

2006

ገጠር

50226

49425

99651

95.28

ከተማ

2344

2592

4936

4.72

ድምር

52570

52017

104587

100

2007

ገጠር

50882

46395

97277

94.01

ከተማ

2822

3374

6196

5.99

ድምር

53703

49770

103473

100

የጥገኝነት ምጣኔ/Dependency Ratioየወረዳዉ ህዝብ ብዛት 2007 .=103473 15 አመት በታች 41885 ፣ከ64 አመት በላይ5400 ፣ከ15-64 አመት 56188 ሲሆን

የወረዳዉ ዋና ከተማ አጣዬ ሲሆን ከአዲስ አበባ ደሴ ዋናዉን አስፋልት በማቋረጥ በመመስረቱ ለልማት በክልሉ የተመረጠዉ በኢንዱስትሪ ቀጠና ኮምቦልቻ አካባቢ የምትገኝ ቆላማ የአየር ንብረት ያላት ሲሆን በጥቅሉ ወረዳዉ በበልግና በመኸር ዝናብ ተጠቃሚ እንዲሁም በመስኖ ልማት እንቅስቃሴ የተሻለ አካባቢ ከመሆኑም ባሻገር 6 የገጠር ቀበሌዎችና 1 የከተማ ቀበሌ 24 ሰአት ሙሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ አዉቶማቲክ ስልክና በገጠር ቀበሌዎች ገመድአልባ ስልክ እንዲሁም በወረዳዉ ካሉት የገጠር ቀበሌዎች ከአንዱ በስተቀር በመንገድ የተገናኙ ናቸዉ፡፡

የወረዳዉ መልክአ ምድራዊ ሁኔታ

የኤፍራታና ግድም ወረዳ የቆዳ ስፋት 50113/ ሲሆን የወረዳዉ ጅኦግራፊያዊ መገኛ/Geographical Location/

በሰሜን 10° 25´59´´N &10° 05´ 10 ´´N

በምስራቅ 39° 45´ 88´´  E & 39° 55´ 03´´  N

ከዚህም ዉስጥ ተራራማ 68% ሜዳማ 16% ወጣገባነት 10% ሸለቋማ 6% የቆዳ ሽፋን ይይዛል፡፡የወረዳችን 50113 / መሬት አቀማመጥ በአግሮክላይሜቲክ ዞን ከፋፍለን ስንመለከት ቆላማ 8018//16%/ ወይና ደጋማ30017/62%/ ደጋማ 11025/22%/ የቆዳ ሽፋን ሲሆን ዉርጭ የለም

የወረዳዉ አማካኝ ዓመታዊ የዝናብ መጠን 950.9 . ሲሆን የሙቀት መጠኑ 12-24 °c/ድግሪ ሴልሽየስ/ነዉ፡፡የወረዳዉ ከፍታ ከባህር ወለል በላይ 1140-3200 ሜትር ከፍታ አለዉ፡፡የአፈር አይነቱን ስንመለከት ቀይ አፈር 39%ጥቁር አፈር 37%ቡናማ አፈር 6% ግራጫ 18 ይሸፍናል፡፡በወረዳዉ ዉስጥ መጠነኛ የሚባሉ ወንዞች ያሉ ሲሆን ለአርሶ አደሩ ለመስኖ ስራ የሚጠቅሙ ናቸዉ፡፡

ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ

አብዛኛዉ የወረዳቸችን ህዝብ እንደሌሎች የሀገራችን ክፍሎች 85% በላይ የሚሆነዉ የወረዳዉ ህዝብ በገጠር የሚኖር ሲሆን የህዝቡ ዋነኛ መተዳደሪያ 83% በእርሻ ሲሆን 4% በእደ ጥበብ ዘርፍ የሚተዳደሩ፣10% በንግድ ስራ፣2%በቀን ስራ፣1% በቅጥር ተሰማርተዉ ይገኛሉ፡፡የተለያዩ እምነት ያላቸዉ የህ/ሰቡ ክፍሎች በመፈቃቀር፣በመከባበር፣በመቻቻል ይኖሩበታል፡፡ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንደሚከተለዉ ከግብርናዉ ዘርፍ ተነስተን እንመለከታለን፡፡

ትምህርት

ልማትን ለማፋጠን እና ድህነትን ለመቀነስ ለትምህርት ትኩረት መስጠት እንዳለብን ሁሉ ከትምህርት እርከኖች ደግሞ ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በተለይ ለሴቶች ተሳትፎ ቅድሚያ ትኩረት መስጠት የበለጠ ጠቃሚ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡በመሆኑም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ለማስፋፋት መደበኛና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች በመታገዝ መሰረታዊ ትምህርትን ለሁሉም ዜጋ ማዳረስ እና ሴቶችን የበለጠ ተሳታፊ ማድረግ የተመቻቸ ቤተሰብ ለመፍጠር ይረዳል

ከዚህ አንፃር ወረዳችን ለዚህ ዓቢይ ተግባር ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የት/ እድገት የሚያመለክቱ መረጃዎች እንደሚቀጥለዉ አቅርበናቸዋል፡

 

የት/ ተቋማት ብዛት በየ ዓመቱ

የት/ ዘመን

አጸደ

ህጻናት ብዛት

1-8

የተቋማት ብዛት

አጠቃላይ 2 //ፕሮግራም

የከፍተኛ መሰናዶ /ቤት

/ ፕሮግራም

2005

3

60

1

1

2006

3

60

1

1

2007

3

60

2

1

የጤና አገልግሎት

የአንድ ሀገር ማህበራዊ እድገት አመልካች ከሆኑት ወስጥ ጤና አንዱ ነዉ፡፡ የጤና አገልግሎት ማግኘት ሰብአዊ መብት ከመሆኑም በላይ ጠቀሜታዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ይህም ምርታማነትን ለማሳደግና እድገትን ለማፋጠን ሆነ ለማምጣት አጋዥ ነዉ፡፡ እነዚህን ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት በወረዳችን መንግስት የነደፋቸዉን የጤና ፕሮግራሞች ተግባራዊ በማድረግ የማህበረሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል እና ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር እስከ አሁን ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት በጤናዉ ረገድ የላቀ ለዉጥ እየተመዘገበ ይገኛል፡፡

 

.

የተቋማት ብዛት እና የህዝብ ጥምርታ

ተቋማት

ጤና ኬላ

ጤና ጣቢያ

2004

የጤና ተቋማት ህዝብ ጥምርታ

6749

20247

የጤና ተቋማት ብዛት

18

6

2005

የጤና ተቋማት ህዝብ ጥምርታ

5000

25000

የጤና ተቋማት ብዛት

19

6

2206

የጤና ተቋማት ህዝብ ጥምርታ

5000

25000

የጤና ተቋማት ብዛት

20

6

2007

የጤና ተቋማት ህዝብ ጥምርታ

5000

25000

የጤና ተቋማት ብዛት

20

6

ግብርና ገጠር ልማት

በወረዳዉ ዉስጥ ቀዳሚዉን ስፍራ የሚይዘዉ የግብርናዉ ዘርፍ ሲሆን አርሶ አደሩ የሰብል ምርትን ከማምረት ባሻገር የእንሰሳት እርባታንም ጎን ለጎን በማካሄድ ልማትን በማፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ወረዳዉ የበልግና የመኸር ዝናብ ተጠቃሚ እንደመሆኑ ሁለቱም ወቅቶች የሰብል ልማት ይከናወናል፡፡

ሰብል ምርት

Ø በወረዳዉ የሚበቅሉ ዋና ዋና ሰብሎች

የብዕር፡-ጤፍ፣ ገብስና ስንዴ

የአገዳ፡- በቆሎ፣ዘንጋዳ፣ማሽላ

ጥራጥሬ፡-ባቄላ፣አተር፣ሽንብራ፣ምስር፣ማሾ፣ቦለቄ፣አብሽ

አትክልት፡-ጎመን፣ጥ/ጎመን፣ቆስጣ፣ቀይስር፣ካሮት

ፍራፍሬ፡አፕል፣ፖም፣ማንጎ፣ዘይቶ፣መንደሪን፣ሎሚ፣ትርንጎ፣ፓፓያ፣ሙዝ የመሳሰሉት ይበቅላሉ፡፡

በወረዳው በሰብል ላይ የሚከሰቱ ዋና ዋና ተባዮች

ተምች አንበጣ፣ግሪሳ፣ጥናዚዛ፣ፌንጣ፣ሳይትል፣ቀይ የጤፍ ትል፣አገዳ ቆርቁርና ክሽክሽ/apids/ በዋናነት ይጠቀሳሉ

በወረዳው በሰብል ላይ የሚከሰቱ ዋና ዋና በሽታወችን ስንመለከት

ዋግ፣አረማሞ፣ስርአበስብስ፣ፓውደሪ፣በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

መስኖ ልማት

መስኖ ልማት እንደ ወረዳችን ካለው የልማት አቅም /potential/አንፃር ብዙ የሚጠበቅብን ቢሆንም በአሁኑ ሰአት /አደሩ በሂደት ከባለፈው ዓመታት አንፃር ሲታይ 2-3ጌዜ በመስኖ የማምረት ልምድ እየዳበረና እየተሻሻለ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ በተጨባጪም እየታየ ይገኛል፡፡

በዚህም ዝናብን ብቻ አንጋጦ እየጠበቀ ያመርት የነበረዉ የወረዳችን /አደር በብዙ መልኩ እንደተለወጠና ኑሮዉ እየተሸሻለ መምጣቱ በየአመቱ ግንባር ቀደም ተሸላሚ ቁጥር መጨመሩና መለወጡ አይነተኛ ምሳሌ ነዉ፡፡

ለዚህ እድገት መገኘት እንደ ዋና ዋና ምክንያት የሚጠቀሱት

· አርሶ አደሩ በዝናብ ብቻ ማምረት አስተማማኝ ያለመሆኑን ከባለሙያዎቹ የሚያገኘው የኤክስቴንሽን ምክር አገልግሎትና ከመንግስት ትኩረት አቅጣጫ ጋራ በአመራሩ እየተደጋገመ ያለው ዕገዛ ጋር ተያይዞ /አደሩ የአስተሳሰብ ለውጥ በተጨባጪ እየመጣ መሆኑ

· በተለይም በገበያ ተኮር ምርት ለምሳሌ ልዩ ልዩ በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ በአጪር ጊዜ አምርቶ ገቢውን እያሻሻለ መምጣቱ

· በመንግስት አጋዝነት ልዩ ልዩ እገዛ በተለይም የምርት ማዳበሪ ግብዓት ለምሳሌ ዳፕ፣ዩሪያ፣የውሃ መሳቢያ ሞተር መሳሰሉትን በተፈለገው በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረባቸው ፡፡

· በባህላዊና በዘመናዊ ወንዝ እና የመስኖ ክፍል ግንባታ በመንግስት በአጋዥ ድርጅቶች ግንባታ መሰራታቸው ለመስኖ ልማት ምቹ ሁኔታ መፈጠር

· ልዩ ልዩ ስልጠና የህዝብ ኮንፈረንስ በቀበሌና በወረዳ ለአ/አደሩ መሰጠቱ በዋነኛነት ለመስኖ ልማት ዕድገት መገኘት ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

 

Last Updated (Friday, 09 December 2016 14:28)